ጥር 15፣ 2018 ታሪካዊው ዋቢ ሸበሌ ሆቴል ለሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ተሸጠ። በኢትዮጵያ የቱሪዝም ዘርፍ ውስጥ በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሰውና የአዲስ አበባ መለያ ምልክት የሆነው ዋቢ ሸበሌ ሆቴል፣ በዛሬው እለት በይፋ ለሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ተላለፈ። ይህ ታላቅ የንግድ ስምምነት በከተማዋ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ላይ አ...