ታኅሣሥ 18፣ 2018 ኢትዮጵያ በዙሪያዋ ያሉ ወደቦችን በባቡር ለማገናኘት የ5 ሺህ ኪሎ ሜትር መስመር ጥናት ማጠናቀቋን ይፋ አደረገች በርበራን፣ ሞምባሳን፣ ጂቡቲና ፖርት ሱዳንን ጨምሮ በዙሪያዋ ያሉ ሁሉንም ወደቦች በባቡር መስመር ለማገናኘት ያቀደውን ፕሮጀከት ጥናት በኢትዮ-ጂቡቲ ባቡር ትራንስፖርት ባለሙያዎች መሠራቱን የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክ ሚኒስቴር አስታውቋል።