ታኅሣሥ 29፣ 2018 በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ የተካሄደው 3ኛው ዙር "የአእላፋት ዝማሬ" በታላቅ ድምቀት ተጠናቀቀ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓል (ገና) ዋዜማ ምክንያት በማድረግ ያዘጋጁት 3ኛው ዙር "የአዕላፋት ዝማሬ" መርሐግብር በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ በሰላም መጠናቀቁ ተገለ...