ታኅሣሥ 19፣ 2018 ዓለማችን የመጀመሪያውን ስክሪን አልባ ላፕቶፕ (Spacetop G1) አስተዋወቀች የቴክኖሎጂው ዓለም በየቀኑ አዳዲስ ፈጠራዎችን እያስተናገደ ባለበት በዚህ ወቅት፣ ሳይትፉል የተሰኘው ኩባንያ "Spacetop G1" የተሰኘውን እና ምንም ዓይነት አካላዊ ስክሪን የሌለውን ላፕቶፕ ለገበያ ማቅረቡን አስታውቋል።