የቡርኪናፋሶ መንግሥት፣ ውሳኔው በቅርቡ አሜሪካ በቡርኪናፋሶ ዜጎች ላይ የጣለችውን እገዳ ተከትሎ የመጣ መሆኑን አስታውቋል፡፡
የአገሪቱ ባለሥልጣናት፤ እርምጃው ሉዓላዊነትን ለማስፈንና በአለም አቀፍ ግንኙነቶች ፍትሃዊነትን ለማረጋገጥ ያለመ ነው ብለዋል፤ የትኛውም ሀገር ያለአግባብ ኢላማ መሆን እንደሌለበት አጽንኦት በመስጠት፡፡
ቡርኪናፋሶ ከዋሽንግተን ጋር ያለው ዲፕሎማሲያዊ ውዝግብ እየጨመረ በመጣበት በዚህ ወቅት፣ ተመሳሳይ የአጸፋ እርምጃ እየወሰዱ ያሉ የሳህል ሀገራትን ተቀላቅላለች ተብሏል፡፡