እስከ 85 ዓመታቸው ስልጣን ላይ መቀመጥ የሚያስችላቸውን ምርጫ እንዳሸነፉ የተነገረላቸው የ81 ዓመቱ አዛውንት ሙሴቬኒ ዋነኛ ተፎካካሪያቸው የነበረው የቀድሞ ሙዚቀኛና ፖለቲከኛ ቦቢ ዋይን ነበር።
ዋይን ከምርጫው በኋላ ለደኅንነቱ በመስጋት ተደብቆ ይገኛል።
![Commander of the Ugandan Armed Forces, General Muhuzi Kainerugaba [Wikipedia]](http://dne.lememar.com/storage/news/Ugandan%20Armed%20Forces,%20General%20Muhuzi%20Kainerugaba.jpg)
የሙሴቬኒ ልጅ ጄነራል ካይኔሩጋባ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ ዋይን በ48 ሰዓታት ውስጥ እጁን እንዲሰጥ አዘዋል።
ቦቢ ዋይን ፕሬዝዳንት ሙሴቬኒ በ81 ዓመታቸው ለ7ተኛ ጊዜ ያሸነፉበት ምርጫ ውጤት ይፋ ከመሆኑ በፊት የመንግሥት ፀጥታ ኃይሎች ከቤቱ ሊይዙት ሲመጡ ማምለጡን እና ተደብቆ እንደሚገኝ ተነግሯል።
ዋይን በምርጫው በከፍተኛ የድምጽ ብልጫ በሙሴቬኒ ተበልጦ ሁለተኛ መሆኑ ከመገለጹ በፊት ምርጫው መጭበርበሩን የሚገልጹ ተደጋጋሚ መግለጫዎችን በማውጣት ሕዝቡን ለሰላማዊ ተቃውሞ ጠርቷል።
ጄኔራሉ የአባታቸው ሥልጣን ተረካቢ ይሆናሉ ተብሎ በስፋት የሚታመን ሲሆን፣ ለተቃዋሚው ፖለቲከኛው ጠንከራ ማስጠንቀቂያ አስተላልፈዋል።
ቦቢ ዋይን " በ48 ሰዓታት ውስጥ እጁን ለፖሊስ የማይሰጥ ከሆነ እንደ ሕገወጥ/አመጸኛ ተቆጥሮ እርምጃ ይወሰድበታል " ሲሉ ዝተዋል።
ጄነራሉ በሌላ መልዕክታቸው " ካለፈው ሳምንት ወዲህ 22 የኤንዩፒ (የቦቢ ዋይን ፓርቲ) ሽብርተኞችን ገድለናል " ሲሉ እርምጃ መወሰዱን ገልጸዋል።