በግድቡ ምክንያት 55 ቢሊዮን ሜትር ኩብ የነበረው የግብፅ የውሃ ድርሻ 38 ቢሊዮን ሜትር ኩብ ቀንሶ 17 ቢሊዮን ሜትር ኩብ መግባቱን በመጥቀስ፣ የሀገራቸውን ጉዳት ለግብፅ ሴኔት አስረድተዋል። የግብፅ የውሃ ድርሻ 55.5 ቢሊዮን ሜትር ኩብ ሀገሪቱ የውሃ ድርሻ ወደ 88.5 ቢሊዮን ሜትር ኩብ ማሻቀቡንም ገልፀዋል፡፡
የግብጽ ባለሥልጣናት ተደጋጋሚ መግለጫዎች፣ የቅኝ ግዛት ዘመን ስምምነቶችን በመጥቀስ፣ "ታሪካዊ መብቶች" ላይ መተማመናችውን የሚያሳይ ነው ሲል የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከዚህ ቀደም ባወጣው መግለጫ ኮንኗል፡፡
“ከኢትዮጵያ ደጋማ ቦታዎች የሚመነጨው አባይ ወንዝ፣ የናይል ተፋሰስን 86 በመቶ ውሃ ያዋጣል። የአባይ ተፋሰስ ውሃ የኢትዮጵያ 70 በመቶ የገጸ ምድር ውሃ ነው፤” ብሏል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ ግድቡ የተገነባው የጥቁር ሕዝብ ታሪክን ለመቀየር እንጂ በፍጹም ወንድሞቿን ለመጉዳት አለመሆኑን በግድቡ የምርቃት ሥነ ስርዓት ላይ አረጋግጠዋል፡፡
ሱዳን በበኩሏ፤ ግድቡ ለግብርና እና ለኤሌክትሪክ የሚሰጠውን ጥቅም ብታምንም፣ ከግድቡ የሚለቀቀው የማስተንፈሻ ውሃ የወንዝ ሙላትና የጎርፍ ማጥለቅለቅ አስከትሏል ስትል ኢትዮጵያን ከስሳለች፡፡
በመስከረም ወር መጨረሻ ጉዳዩን አስመልክቶ የተጠየቁት የኢትዮጵያ ውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ሀብታሙ ኢተፋ፤ የሕዳሴ ግድብ የሱዳንን ጎርፍ ለመቀነስ መርዳቱን ጠቅሰው፤ “ትርፍ ውሃ አልለቀቅንም” ብለዋል። ለሱዳን ጎርፍ ኢትዮጵያን ተጠያቂ የማድረግ የግብፅ ሀሰተኛ ውንጀላንም መሠረተ ቢስ መሆኑን ኢትዮጵያ አስታውቃለች ሲል ስፑትኒክ አስታውሷል፡፡