የኒውዮርክ ገዢ ኬቲ ኦቹል "የኒውዮርክ ነዋሪዎችን ደህንነት መጠበቅ ቅድሚያ የምሰጠው ነገር ነው ይህም ልጆቻችንን ከመጠን በላይ እንዲጠቀሙ ከሚያበረታቱ የማህበራዊ ሚዲያ ጎጂ ገጽታዎች መጠበቅንም ይጨምራል" ብለዋል።
የኒውዮርክ አዲሱ ህግ ሱስ የሚያሲይዙ እና " Auto play or infinite scroll" ባላቸው መተግበሪያዎች ላይ የሚተገበር ነው ተብሏል።
በአንድ የህጉ ጥሰትም ኒውዮርክ የ5000 ዶላር ቅጣትን እንደምትቀጣ ገልፃለች።
አዲሱ የኒውዮርክ ህግ በሲጋራ ላይ እንደሚፃፈው ጎጂ ነው የሚል አይነት መልዕክትን በማህበራዊ ሚዲያ ለማምጣት ያለመ ነው።
ማህበራዊ ሚዲያ የበርካቶችን በተለይ የታዳጊዎችን የአዕምሮ ጤና እየፈተነ ሲሆን በዚሁ ምክንያት በቅርቡ አውስትራሉያ ከ16 አመት በታች የሆኑ ህፃናት የማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ ማገዷ ይታወሳል።