እስከ ዛሬ ባለው አሰራር የጂሜል ተጠቃሚዎች አንዴ የመረጡትን የኢሜይል አድራሻ መቀየር የማይችሉ ሲሆን፣ አዲስ ስም ለመጠቀም አዲስ አካውንት መክፈት ግዴታ ነበር።
ይህም ተጠቃሚዎች የቆዩ መረጃዎቻቸውን እና መልዕክቶቻቸውን ወደ አዲሱ አድራሻ ለማዘዋወር ለከፍተኛ እንግልት ሲዳርጋቸው ቆይቷል።
አዲሱ የቴክኖሎጂ ለውጥ ተጠቃሚዎች የነበራቸውን መረጃ ሳይለቁና አዲስ አካውንት መክፈት ሳያስፈልጋቸው፣ በነባሩ አካውንታቸው ላይ ስማቸውን ብቻ ማስተካከል እንዲችሉ ዕድል እንደሚሰጥ ይጠበቃል።
ይህ ማሻሻያ በተለይ በወጣትነት እድሜያቸው ፕሮፌሽናል ያልሆኑ ስሞችን ሲጠቀሙ ለነበሩና አሁን ላይ ስማቸውን መቀየር ለሚፈልጉ ተጠቃሚዎች ትልቅ እፎይታን እንደሚሰጥ ተነግሯል።
ጎግል ይህን አገልግሎት መቼ በይፋ እንደሚጀምር እስካሁን የተቆረጠ ቀን ባይገልጽም፣ በቅርቡ ተግባራዊ እንደሚሆን መረጃዎች ያመለክታሉ።