የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአሁኑ ሰዓት በደሴ እና አካበቢዋ ባለው ለበረራ አመቺ ያልሆነ የአየር ፀባይ ምክንያት በዛሬው እና በነገው ዕለት ወደ ከተማዋ የሚያደርገውን በረራ ለማቋረጥ መገደዱን አሳውቋል።
አየር መንገዱ ከሚቲዎሮሎጂ በሚደርሰው መረጃ መሰረት የአየር ፀባዩ እንደተስተካከለ በረራዎቹ ወደመደበኛ አገልግሎታቸው የሚመለሱበትን ጊዜ እንደሚያሳውቅ ገልጿል።
በአገልግሎቱ መቋረጥ ለሚፈጠረው መጉላላት ይቅርታም ጠይቋል።