አሁን ያለው የጉምሩክ አዋጅ ለበርካታ ዓመታት ያገለገለ በመሆኑ፣ የአዋጁን ድንጋጌዎች ዓለም አቀፍ የንግድ እንቅስቃሴ ከደረሰበት የዕድገት ደረጃ ጋር ማስማማት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል።
ይህ የማሻሻያ አዋጅ በዋናነት በሀገሪቱ እያደገ የመጣውን የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ልማት ለመደገፍና ሕጋዊ የንግድ እንቅስቃሴን ለማሳለጥ ታቅዶ የተዘጋጀ ነው።
በተጨማሪም የኢንቨስትመንት ምህዳሩን ይበልጥ ማራኪ ለማድረግና የጉምሩክ አሰራሩን ዘመናዊ ከሆነው ዓለም አቀፍ የንግድ ሥርዓት ጋር ለማቀናጀት ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ተገልጿል።
ምክር ቤቱ በማሻሻያ አዋጁ ላይ በሰፊው ከተወያየና አስፈላጊ ግብዓቶች እንዲካተቱ ካደረገ በኋላ፣ ረቂቅ አዋጁ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምፅ ውሳኔ አሳልፏል።
ይህ ማሻሻያ መጽደቁ የሀገሪቱን የንግድ ፍሰት በማቀላጠፍና የኢኮኖሚ ተወዳዳሪነትን በማሳደግ ረገድ ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል።